Home » Archives by category » የኢሳት አማርኛ ዜና (Page 41)

የመንግስትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ፍጥጫ ቀጥሎአል

የመንግስትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ፍጥጫ ቀጥሎአል

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለመንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጣቸው ግፊት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በዛሬው እለት የአርብን ጸሎት ምክንያት በማድረግ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአወልያ መስጊድ ተገኝተው እንደነበር በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። ሙስሊሞቹ ከዚህ ቀደም ላቀረቡት የመብት ጥያቄ የመንግስትን መልስ ከተወካዮቻቸው ለመስማት በብዛት ቢገኙም፣ የጠበቁትን መልስ ለማግኘት አልቻሉም።…

አንድነት በሊዝ አዋጁ ዙሪያ እሁድ ውይይት ያደርጋል

አንድነት በሊዝ አዋጁ ዙሪያ እሁድ ውይይት  ያደርጋል

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ የጠራው ስብሰባ በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚካሄድ ዶ/ር ነጋሶ ገለጡ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለኢሳት እንደገለጡት ፓርቲያቸው ህዝቡን በአገሩ መሬት አልባ እና ንብረት አልባ የሚያደርገውን አዋጅ አጥብቀው ይቃወማሉ። 3፡55-4፡34 ባለፈው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ የአፍሪካ…

ተመድ የኢትዮጵያን መንግስት ድርጊት ኮነነ

ተመድ የኢትዮጵያን መንግስት ድርጊት ኮነነ

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ህጉ  የህዝብን መብቶች አላግባብ ለማፈን በጥቅም ላይ መዋል እንደሌለበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ የመንግስታቱ ድርጅት ገለልተኛ የሰብኣዊ መብት የባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ያለአግባብ በመወንጀልና እስራት በመፍረድ የፀረ ሽብር ህጉን በመጠቀም  የህዝብን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማፈን መንግሰት የሚፈፅመዉን ተግባር አውግዘዋል። “የመንግሰት…

በሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ እራሷን አጠፋች

በሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ እራሷን አጠፋች

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንዲት የ23 አመት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ በጋዲር ከስሩዋን በአሰሪዎቿ መኖሪያ ቤት ዉስጥ እራሷን በመስቀል ህይወቷን ማጥፋቷን የሊባኖስ ዴይሊ ስታር ገለፀ። ሳባ ማሩን በተባለዉ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ተሰቅላ ስለተገኘችዉ ኢትዮጵያ አሟሟት ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አሰሪዋ ራሚ አቡ ካሊል ለፀጥታ ሃይሎች ቃሉን…

በዋካ ከተፈጠረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት ወጣቶች በገደብ ተፈቱ

በዋካ ከተፈጠረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት ወጣቶች በገደብ ተፈቱ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት ወራት በዋካ ከተፈጠረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩት ወጣቶች በገደብ ተፈቱ፣  ወጣቶችን በግንቦት 7 ስም ለመክሰስ ተዘጋጅቶ የነበረው ክስ በወጣቶቹ ጥንካሬ እንዲከሽፍ ተደርጓል። ለነጻነት ሰመአቱ የኔሰው ገብሬ ህልፈት ምክንያት የሆነው ፣ የዋካ ወጣቶች እስር የመንግስትን የፍትህ ስርአት ያጋለጠ እንደነበር የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት…

“አገራችንን ከወድቀት ለማዳንና አንድነቷን አስጠብቆ ለማስቀጠል አሁኑ ተነስተን በጽናት እንታገል” ሲል አንድነት ጥሪ አቀረበ

“አገራችንን ከወድቀት ለማዳንና አንድነቷን አስጠብቆ ለማስቀጠል አሁኑ ተነስተን በጽናት እንታገል” ሲል አንድነት ጥሪ አቀረበ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “አገራችንን ከወድቀት ለማዳንና አንድነቷን አስጠብቆ ለማስቀጠል አሁኑ ተነስተን በጽናት እንታገል” ሲል አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ። “አገርን ከውድቀት መታደግ፤የወቅቱ አንኳር ጥያቄ ነው”በሚል ርዕስ አንድነት ባወጣው መግለጫ፤ “ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ በህልውናዋ ፀንታ የቆየችውን ይህችን አገር የዛሬዎቹ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሲሸራርፏትና ለባዕዳን አሳልፈው ሲሸጧት…

በሙስሊም ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ያለውን መጅሊስ ለመታደግ፤ ኢህአዴግ “በሽምግልና” ስም ጣልቃ መግባቱ ተሰማ

በሙስሊም ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ  እየደረሰበት ያለውን መጅሊስ ለመታደግ፤ ኢህአዴግ  “በሽምግልና” ስም  ጣልቃ  መግባቱ ተሰማ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስሊም ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ  እየደረሰበት ያለውን “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት” (መጅሊስ) ለመታደግ፤ ኢህአዴግ  “በሽምግልና” ስም  ጣልቃ መግባቱ ተሰማ። በኢህአዴግ ሸምጋይነት በዛሬው ዕለት በመጅሊሱ መሪዎች እና ብዙሀኑን ምእመን በሚወክሉት ጊዜያዊ ወኪሎች መካከል ሊደረግ የነበረው ውይይት፤ ሳይካሄድ ቀርቷል። በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በሽፈራው ወልደማርያም እና በሚኒስትር ጁነዲን…

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሶማሊያን ጎበኙ

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሶማሊያን ጎበኙ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ዊሊያም ሄግ የሶማሊያ ዋና ከተማ በሆነቸው ሞቃዲሾ የተገኙት  በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ነው። የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች በሶማሊያ መረጋጋት እንዲፈጠር ጦራቸውን እንዲልኩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ከሁለት ሳምንት በሁዋላ እንግሊዝ በሶማሊያ ጉዳይ የሚመክር አንድ አለማቀፍ ውይይት አዘጋጅታለች። በውይይቱ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ…

አንድ ፖሊስ ጥር 21 ቀን የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በዓል በሚከበርበት ዕለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት ጉዳት ደረሰ

አንድ ፖሊስ ጥር 21 ቀን የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በዓል በሚከበርበት ዕለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት ጉዳት ደረሰ

ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ አንድ የወረዳው ፖሊስ የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በአል በሚከበርበት እለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት አንድ ሰው ወዲያውኑ ሲሞት ፣ በርካቶች በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ የኢሳት የጋሞጎፋ ዞን ወኪል እንደዘገበው በጨንጫ ወረዳ የአስቴርዮ ማርያም በአል ከፍተኛ ህዝብ ተገኝቶ የሚያከብረው ሀይማኖታዊ ክብረ…

አዲሱ የሊዝ አዋጅ በክፍለ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ፈጥሯል

አዲሱ የሊዝ አዋጅ በክፍለ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ፈጥሯል

ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደዘገቡት፣ የኑሮ ውድነቱ የፈጠረው ውጥረት ሳይበርድ አሁን ደግሞ የሊዝ አዋጁ መጨመሩ ህዝቡ አለመረጋጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በኦሮሚያ የሚኖሩ ሰው ሲናገሩ በእርሳቸው አካባቢ አዲሱ የመሬት ፖሊሲ የህዝብ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው። ነገሮች ሊፈነዱ ተቃርበዋል የሚሉት እኝሁ ግለሰብ…