Home » Archives by category » የኢሳት አማርኛ ዜና (Page 3)

በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ በሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ

በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ በሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲናዶስ፤  በአርሲ-አሰሳ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሙስሊሞች ላይ የኢህአዴግ ታጣቂዎች  ተኩስ በመክፈት  የፈፀሙትን ግድያ አጥብቆ አወግዟል። ሲኖዶሱ  በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ግድያ እና አሁንም እየተፈፀመ ያለውን  በደል ያወገዘው ሰሞኑን ያካሄደውን 33 ኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው።…

ካናዳ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ልትቀንስ ነው

ካናዳ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ልትቀንስ ነው

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወግ አጥባቂው የካናዳ መንግስት  ለውጪ እርዳታ ከሚሰጠው ገንዘብ ውስጥ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት  377 ሚሊዮን ዶላር ለመቀነስ መወሰኑን “ኦታዋ ሲቲዝን”ዘገበ። የካናዳ ዓለማቀፍ የልማት ፕሮግራም -ሲ.አይ.ዲ.ኤ፤ የሁለትዮሽ ፕሮግራሙን ከሚቀንስባቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ  ሆና መለየቷን የካናዳ ዓለማቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቤቭ ኦዳ ገልጸዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ ከምታገኘው እርዳታ…

ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ ትሆናለች ተባለ

ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ ትሆናለች ተባለ

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር አይኤም ኤፍን ጠቅሶ እንደዘገበው ኤርትራ በማእድን፣ በመሰረተ ልማት እና በእርሻው መስክ ባስመዘገበችው ውጤት ከምስራቅ አፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ አገር ትሆናለች። ኤርትራ በ7.5 በመቶ እንደምታድግ የተነበው አይ ኤም ኤፍ፣ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 5 በመቶ ብቻ ያድጋል ብሎአል። የመለስ መንግስት 11 በመቶ…

አቶ ክፍሌ ስንሻው በማረሚያ ቤት አረፉ

አቶ ክፍሌ ስንሻው በማረሚያ ቤት አረፉ

ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በሀገር ክህደትና ህገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ አሲረዋል ተብለው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው በቃልቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክፍሌ ስንሻው በትላንትናው እለት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡ በዛሬው እለት አስከሬናቸው ከፖሊስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ ሚንሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ሄዷል…

በእነ አቶ አንዷለም አራጌ ላይ ሊሰጥ የነበረው ውሳኔ ተላለፈ

በእነ አቶ አንዷለም አራጌ  ላይ ሊሰጥ የነበረው ውሳኔ ተላለፈ

ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ዐቃቤ-ሕግ በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ከከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላትና ጋዜጠኞች ውስጥ በሀገር ውስጥ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን የሚከላከሉት ስምንት ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ለውሳኔ ዛሬ ጠዋት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቢቀርቡም ፍርድ ቤቱ በተለዋጭ ቀጠሮ ለሰኔ 14 ቀን 2004…

የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተቃውሞ ለአደረጉ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ

የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተቃውሞ ለአደረጉ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ

ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትናንት ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን  ፆማቸውን በመዋል ተቃውሞ በማሰማት ላይ ላሉት  የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ። ተማሪዎቹ፤ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሙስሊም  ሀይማኖታዊ መብቶቹን ለማስከበር እያደረገ ያለው ትግል የነሱም ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ፤ መብታቸው እስኪከበር ድረስ  ከሙስሊም ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን እንደሚሰለፉ ገልጠዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ…

ኢህአዴግ መጅሊስ እንዲፈርስ ቢወሰንም ሙስሊሞቹ ግን ትግሉ ይቀጥላል ይላሉ

ኢህአዴግ መጅሊስ እንዲፈርስ ቢወሰንም ሙስሊሞቹ ግን ትግሉ ይቀጥላል ይላሉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተፈጠረበት ጫና ሃይማኖቱን በበላይነት ሲመራ የነበረውንና በመንግሥት የሚደገፈውን መጅሊስ እንዲፈርስ ባለፈው ሃሙስ ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በመጅሊስ የተጠሩ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች ከፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን ከሰኔ መጀመሪያ እስከ…

አንድነት ፓርቲ መንግስት ያወጣውን የቅድመ ምርመራ ህግ እንዲያነሳ ጠየቀ

አንድነት ፓርቲ መንግስት ያወጣውን የቅድመ ምርመራ ህግ እንዲያነሳ ጠየቀ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ዛሬ ” ከመቃብር ተመልሶ የመጣውን የሳንሱር መቀስ እንቃወመዋለን ወደ መቃብሩ እንዲመለስም እንታገለዋለን ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ብርሀንና ሰላም ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን በማስመሰል ካዘጋጀው ውል ጀርባ ሌላ እጅ እንዳለ ይጠረጠራል በማለት ከገለጠ በሁዋላ፣ አዋጁ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ተብሎ በሚታሰበው ህገ…

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላት በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላት በከፍተኛ  ሙስና ተዘፍቀዋል

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የሚገኙ 32 የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ ተዘፍቀው እንደሚገኙ አንድ ጥናት አረጋገጠ፡፡ የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሸን በተቋማቱ ላይ ያካሄደውን ጥናት በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገበት ወቅት የሰለጠነ የሰው ኃይል በብቃት የማፍራት ኃላፊነት…

የጋምቤላ መንግስት የፖሊስና መካለከያ ሰራዊት ቁጥር እንዲጨመር ጥሪ አቀረበ

የጋምቤላ መንግስት የፖሊስና መካለከያ ሰራዊት ቁጥር እንዲጨመር ጥሪ አቀረበ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የኢሳት የጋምቤላ ዘጋቢ ኡጁሉ ኦሞድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ኦሞድ ኦቦንግ ለአቶ መለስ ዜናዊ፣ ለኢህአዴግ ጽህፈት ቤት፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለፌደራል ፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት በላኩት ደብዳቤ፣ የጋምቤላ የጸጥታ ችግር ከክልሉ መንግስት አቅም በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ…